
Y


የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ተቋም በ2016 ዓ.ም የተግባር ግብ ስምምነት ዙሪያ ለጽ/ቤት ኃላፊዎች ግንዛቤ ሰጠ!





የወራቤ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ “ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ለአባላት ለመስጠት ለጠቅላላ አመራሩ ኦረንቴሽን ተሰጠ!!



በሴቶች ላይ የሚደርሱ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳቶችን በመከላከል የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ!
ታህሳስ 5/2016 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] የወራቤ ከተማ አስተዳደር ሴቶች እና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት በሴቶች ልማት ቡድን አደረጃጀት እና በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።
ተቋሙ በቅርብ ወቅት የሴቶች የልማት ቡድን አደራጅቶ ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ከባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ ማካሄዱ ይታወሳል። ታዲያ በአዲስ መልኩ የተደራጀውን የሴቶች የልማት ቡድን ወደ ተግባር በመቀየር የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል ነዉ የተባለው።
በዕለቱም አዲሱን የሴቶች ልማት ቡድን አደረጃጀት ማጽደቅ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣውን የጋብቻ ፍቺን ለመቀነስ እንዲሁም ልመናን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል።
የሴቶችን አደረጃጀት ማጠናከር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ ባሻገር የሚደርስባቸውን አሉታዊ ጫና በመከላከል ረገድም ወሳኝ ሚና እንዳለዉ ተገልጿል።
በከተማው ከወትሮው በተለየና ባልተለመደ መልኩ የማህበረሰቡን ባህል የማይመጥን የልመና ልማድ እየተስተዋለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህንኑ ተግባር በጋራ በመከላከል ዜጎች በላባቸዉ ለፍተዉና ጥረዉ እንዲበለጽጉ ማድረግ ይገባል ተብሏል።
በማህበረሰቡ ዉስጥ የኑሮ ጫናው እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች ዉጤታማ አለመሆን ለፍቺ መበራከት እንደ ምክንያት የተጠቆመ ሲሆን ፍቺና መሰል ጉዳዮችን አስቀድሞ መከላከልና