ሳምንታዊው የከንቲባ ችሎት እንደቀጠለ ነው!
ግንቦት 17/2015 [ወ.ኮ] የወራቤ ከተማ አስተዳደር ሳምንታዊው የከንቲባ ችሎት እንደቀጠለ ነው።

በከተማው በቅርቡ በተቋቋመው የከንቲባ ችሎት የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችንና ቅሬታዎችን በመቀበል የመፍትሄ አቅጣጫ እየተሰጠበት ይገኛል።

ባለጉዳዩን ከከንቲባው እና ከባለድርሻ አካላቱ ጋር በቀጥታ የሚያገናኘው የከንቲባ ችሎት የሚነሱ ቅሬታዎችን በየደረጃው በመፍታትና እልባት በመስጠት ረገድ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል።
ከሳምንት በፊት ተዋቅሮ ወደ ተግባር የገባው ይህ የከንቲባ ችሎት በሳምንት አንድ ቀን ዘወትር ሐሙስ በስራ ሰዓት ችሎቱ ይሰየማል።
