በወራቤ ከተማ አስተዳደር በከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) የተከናወኑ ፕሮጀክቶች ተጎበኙ!
ግንቦት 12/2015 [ወ.ኮ] የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ያሲን ከሊል፣ የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አብዱልከሪም ሸሳይድን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና ፎካል ፐርሰኖች በከተማው በUIIDP የተከናወኑ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በመስክ ምልከታው በፕሮግራሙ የተከናወኑ፣ በመከናወን ላይ ያሉ የመንገድ፣ ዲችና ሌሎች ግንባታዎችን እንዲሁም የዘገዩ ፕሮጀክቶችን ተንቀሳቅሰው ተመልክተዋል።

የተከናወኑ እንዲሁም በመከናወን ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች አሁን ላይ ለደረሱበት ደረጃ ባርድርሻ አካላቱ ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርግ እንደነበረ የገለጹት የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ያሲን ከሊል ይህ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ዋና ተጠሪ የሆኑት አቶ አብዱልከሪም ሸሳይድ በበኩላቸው በ2014 በጀት ዓመት የነበሩ ጥንከሬዎችን በማስቀጠል እንዲሁም ጉድለቶችን ለይቶ በማረም ወደ ስራ እንደተገባ በመጥቀስ በዘንድሮው በጀት ዓመት የታቀዱ እቅዶችን ለማሳካት ባሉን ቀሪ ጊዜያት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በከተማው በሚሰሩ ፕሮጀክቶች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በየጊዜው የመጎብኘት እንዲሁም ጠንከር ያለ የድጋፍና ክትትል ስራ እንደሚሰራም ነው የተገለጸው።

