የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ተቋም በ2016 ዓ.ም የተግባር ግብ ስምምነት ዙሪያ ለጽ/ቤት ኃላፊዎች ግንዛቤ ሰጠ!

ታህሳስ 7/2016 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በ2016 ዓ.ም የተግባር ግብ ስምምነት ዙሪያ ለተቋማት ኃላፊዎች ግንዛቤ ሰጥቷል፡፡

መድረኩን የመሩት የወራቤ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብዱልከሪም ሸሳይድ ጠንካራ ተቋም በመፍጠር ረገድ የአመራሩ ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸው ተቋማትን በዕውቀት ለመምራትና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት በየጊዜው የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ወደ ተግባር መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ መህቡባ ስራጅ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ በተቋም ደረጃ ከሪፎርም ስራዎች አንጻር በመልካም አስተዳደር፣ በሰው ሀብት ልማት፣ በዘርፈ-ብዙ ተግባራትና በስነ-ምግባር ዙሪያ በተቀመጡ ነጥቦች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይ በድጋፍና ክትትል ወቅት በተገኙ ክፍተቶች ላይ ከአሰራርና መመሪያ አንጻር የሚገኙ ጉድለቶችን ለማረም ለአመራሩ፣ ለሴክተር ባለሙያዎችና ለቀበሌ መዋቅሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደሚሰጥ ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የፐብሊክ ሰርቪስ ተቋሙ የአሰልጣኞች ስልጠና እንደሚሰጥ የተጠቆመ ሲሆን በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የዕለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡
