በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራ የስራ ሀላፊዎች ቡድን በወራቤ ከተማ አስተዳደር በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ!
ሕዳር 28 /2017 ወራቤ ኮሙኒኬሽን] በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ቡድን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ህንጻ ግንባታ እንዲሁም በከተማው 02 ቀበሌ ዱና አካባቢ እየተገነባ የሚገኘውን ዘመናዊ የመጸዳጀና ሻወር ቤት ግንባታ ሂደት እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

በከተማው 02 ቀበሌ ዱና አካባቢ እየተገነባ የሚገኘውን ዘመናዊ የመጸዳጀና ሻወር ቤት ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጽዱ ኢትዮጵያ በሚል የጀመሩት ኢኒሼቲቭ አካል እንደሆነ ተብራርቷል።

በጉብኝቱ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ያሲን ከሊል፣ የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ አብድልሰመድ አብደላ፣ የወራቤ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ናሲር ቡሽራ፣ የወራቤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የማዘጋጀ ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሻፊ ሙዜ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን የግንባታ ሂደቱ በመልካም አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ተመልክተዋል።
የግንባታ ሂደቱ እንዲፋጠን መስተካከል ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል።



