በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን የሂክማ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ሂደትን ጎበኘ!

ታህሣሥ 2/2017 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችና የመጅሊስ የስራ ኃላፊዎች የሂክማ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡
በማህበረሰብ ተሳትፎና በበጎ አድራጊ ግለሰቦች አነሳሽነት በወራቤ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨርሰቲ የመጀመሪያ ዙር ግንባታው በጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተናግረዋል፡፡
የትምህርትና የእውቀት ተቋማት ብቁና ሀገርን የሚያሻግር ትውልድ የሚገነባባቸው ቦታዎች መሆናቸውን በማንሳት የዩኒቨርሲቲው ግንባታ እንዲጠናቀቅ የዞኑ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል፡፡
በጉብኝት መርሃ ግብሩ የስልጤ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ዋና ሀላፊ ወ/ሮ ነዒማ ሙኒር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይክ ሙሐመድ ኸሊል፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ ኡስታዝ ሳዲቅ ወጌቦ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሂክማ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮችና የመጅሊስ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።