ትውልዱ የጀመረው የባህር በር የማግኘት የሕልውና ጥያቄ ምላሽ እስከሚያገኝ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት – ምሁራን
ትውልዱ የጀመረውን የባህር በር የማግኘት የሕልውና ጥያቄ ምላሽ እስከሚያገኝ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ምሁራን አስገነዘቡ።በአፍሪካ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት እና የፈጣን ኢኮኖሚ ዘዋሪ የሆነችው ኢትዮጵያ ሕልውናዋ የወደቀው በጅቡቲ ኮሪደር ላይ ነው።ኢትዮጵያ በአህጉሩ ከሚገኙ 16 የባህር በር ከሌላቸው ሀገራት አብላጫ የሕዝብ ቁጥር በማስመዝገብ ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች።ከቀይ ባህር 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሀገሪቱ በአንድ የባህር በር […]
የፌደራል የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ አስተዳደር በሶጃት መንደር በራስ አቅምና በባለሀብቶች እየተገነባ ያለውን የእንዲስትሪ መንደርን ጉብኝት አደረጉ!
የፌደራል የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ አስተዳደር በሶጃት መንደር በራስ አቅምና በባለሀብቶች እየተገነባ ያለውን የእንዲስትሪ መንደርን ጉብኝት አደረጉ!መጋቢት 29/2017 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን]የጉብኝቱ አለማ የእንዲስትሪ መንደሩ ወደ ስራ ገብቶ ለዜጎች የስራ እድል እንዲፈጥር የውጭ ምርት የማስገባት ፍላጎትን ለመቀነስ እና ኤክስፖርትን ከፍ ለማድረግ ያለውን አስተዋፆ ማበርከት እንዲቻል ዘንድ ማነቆ የሆኑ የመሰረተ ልማት ችግሮችን በትብብር […]
ከኢትዮ ኮደርስ!
የምሥራች – ነፃ የትምህርት ዕድልለአምስት ሚልዮን ኢትዮጵያዉያንእጅዎ ላይ ባለ ስልክና ታብሌት ጊዜና ቦታ ሳይገድብዎት ተመዝግበዉ በመማር ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ( የተረጋገጠ ) ሠርተፍኬት ያግኙ።ነፃ የኦንላይን ሥልጠናዎቹ ፦- በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣- በዳታ ሳይንስ፣- በዌብ ፕሮግራሚንግ እና- በአንድሮይድ ማበልፀግ ናቸውእርስዎም በመረጡት የትምህርት ዘርፍ በአጭር ጊዜ ተምረዉ ሙያዎን ያዘምኑ፤ ህይወትዎን ወደ ከፍታ ይውሰዱ።ከዓለም ጋር ይነጋገሩ፤ከዓለም ጋር ይስሩ፤ከዓለም ጋር […]
የጤና መድህን ህዝቡን ለህክምና ቋሚ ንብረቱን ከመሸጥ ታድጎታል – የወራቤ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታጁዲን ሁሴን!
መጋቢት 27/2017 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] የጤና መድህን፣ ህዝቡን ለህክምና ቋሚ ንብረቱን ከመሸጥ ታድጎታል ሲሉ የወራቤ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታጁዲን ሁሴን ገለጹ።የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ተግባራዊ መደረጉ የከተማችንን ህዝብ ወደ ህክምና የመሄድ ልምድ በመጨመር፣ የህክምና ተቋማቱንም፣ ታካሚዎችን የማስተናገድና የፋይናንስ አቅማቸው እንዲሻሻል አድርጓል ያሉት አቶ ታጁዲን፣ ተቋማቱ የነበረባቸውን የመድሃኒት አቅርቦትና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በዚህ አመት […]
ከወራቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት!
በከተማችን በከተማ ስታንዳርድ በተመረጡ ቀለሞች ቤቶችን የማስዋብ ሥራ መጀመሩ ይታወቃል።በመሆኑም የተጀመረው የቤቶች የቀለም ቅቢ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን!የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤትመጋቢት 27/2017 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን]
በወራቤ ከተማ የፋይዳ ኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ (National ID) ምዝገባ እየተካሄደ ነው!
መጋቢት 25/2017 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] በወራቤ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መስሪያቤቶች የፋይዳ ኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ (National ID) ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል። ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች የናሽናል ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እንድታደርጉ እና የዘርፉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ከተማ አስተዳደሩ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
የከተማው ጤና ጣቢያ የህዝብ ፎረም መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሄደ!
መጋቢት 25/2017 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] የወራቤ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የሶስተኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ፎረም መድረክ አካሂዷል።የዕለቱን መድረክ የመሩት የወራቤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነስሬ አማን ሁሉን-አቀፍ የጤና ሽፋን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ አቶ ነስሬ አማን አክለውም የከተማዋን የህብረተሰብ ክፍሎችን ከበሽታ መታደግ፤ የጤና […]
“የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” መጋቢት 24 ቀንን በማስመልከት በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ላይ የተለያዩ የማስ ስፖርታዊ ዕንቅስቃሴዎች ተካሄደዋል።
“የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” መጋቢት 24 ቀንን በማስመልከት በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ላይ የተለያዩ የማስ ስፖርታዊ ዕንቅስቃሴዎች ተካሄደዋል። በዕለቱ የተገኙት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ሰባት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ሀገርን የሚያሻግሩ በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል ብለዋል። “ትናንት ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎች እና የነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ቃል […]
በዚህ በጀት ዓመት የሚጠናቀቅና 165 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት በዛሬው እለት በይፋ መጀመሩን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ ገለጹ!
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩና የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ዋና ኃላፊና የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የወራቤ ከተማ ኮሪደር ልማትን በይፋ አስጀምረዋል።
ወራቤ ከተማን ለኮሪደር ልማት ማስጀመሪያ ለማዘጋጀት ሰፋፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ ውሏል!
ታህሣሥ 5/2017 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] በነገው እለት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ክላስተር ከተሞች በይፋ የሚጀመረውን የኮሪደር ልማት ስራ ምክንያት በማድረግ በዛሬው እለት በወራቤ ከተማ በርካታ አካባቢዎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ ውለዋል። በዚህም በከተማዋ ባሉ ልዩ ልዩ ሰፈሮች የሚገኙ መንገዶችን የማጥራት፣ የመንገድ ወሰኖችን ያለፉ ከደረጃ በታች ግንባታዎችን የማስወገድ፣ ዲቾችን የመክፈት፣ ቆሻሻዎችን የማጽዳትና አከባቢዎችን ለስራው ምቹ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል። […]
የወራቤ ከተማ አስተዳደር ለከተማው የህብረተሰብ ክፍሎች የምስጋና መልዕክት አስተላለፈ!
❝መላው የወራቤ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች፡ በከተማችን የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ለማስጀመር ከዲዛይን ጀምሮ በርካታ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።ታዲያ የኮሪደር ልማት ስራውን ተግባራዊ ለማድረግ ከቅድመ ዝግጅቱ ጀምሮ ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ እና ለልማቱ ቅድሚያ በመስጠት ቁርጠኛነታቸውን ላሳዩ ለመላው የከተማው ነዋሪዎች፣ አመራሮች፣ ነጋዴዎች፣ ባለሀብቶች፣ የፀጥታ አካላት፣ ለወጣቶችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀሳብ […]
#የኮሪደር_ልማት_ቅደመ_ዝግጅት_በወራቤ!
በወራቤ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማት ቅድመ-ዝግጅት በተጠናከረ መንገድ እየተሰራ ነው። ታህሣሥ 5 ቀን 2017 ዓ.ም
የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ውጤታማ የልማት ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል – የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ!
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ይህን ያሉት በስልጤ ዞን ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት።
በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን የሂክማ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ሂደትን ጎበኘ!
ታህሣሥ 2/2017 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችና የመጅሊስ የስራ ኃላፊዎች የሂክማ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡በማህበረሰብ ተሳትፎና በበጎ አድራጊ ግለሰቦች አነሳሽነት በወራቤ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨርሰቲ የመጀመሪያ ዙር ግንባታው በጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተናግረዋል፡፡የትምህርትና የእውቀት ተቋማት ብቁና ሀገርን የሚያሻግር ትውልድ የሚገነባባቸው ቦታዎች መሆናቸውን በማንሳት የዩኒቨርሲቲው […]
በወራቤ ከተማ ጤና ጣቢያ ቀልጣፋ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠትና የዲጂታል ስርዓትን ለመዘርጋት በተዘጋጀ ሶፍትዌር ላይ ውይይት ተደረገ!
ሕዳር 30/2017 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] በወራቤ ከተማ አስተዳደር ጤና ጣቢያ ተቋም ቀልጣፋ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠትና የዲጂታል ስርዓትን ለመዘርጋት በከተማ አስተዳደሩ ጤና ጽ/ቤት እና በከተማው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ፍላጎት በተዘጋጀ ሶፍትዌር ላይ ውይይት ተደርጓል።የዲጂታል ስርዓቱ በጤና ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ውስንነቶችን እንዲሁም የተገልጋዩን ማህበረሰብ ጊዜ በመቆጠብ ችግሮችን በመቅረፍ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ጉልህ ሚና […]