Skip to content

በወራቤ ከተማ የሚገኙ ድንቅ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ቅርሶችና መስህቦች

አልከሶ መስጅድ

ALKESO

አልከሶ መስጂድ የሚገኘው በስለጤ ዞን በወራቤ ከተማ አስተዳደር በስተሰሜን አቅጣጫ 8 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ከስልጤ ቀደምት ሀይማኖታዊ መሪዎች አንዱ ለሆኑት አልከሲዬ መታሰቢያነት የተገነባ ጥንታዊና የብሄረሰቡን ስነ-ግንባታ ፍልስፍነ የሚያንፀባርቅ ይዘት ያለው መስጂድ ሲሆን በየአመቱ የረመዳን ፆም ከምግባቱ 15 ቀን ቀደም ብሎ የሚዘጋጀውና በርካታ ባህላዊ ስነ-ስርአቶችን የሚያካትት መውሊድ ይስተናገድበታል፡፡የአልከሶ መስጂድ በአሰራሩም ሆነ ባለው ታሪካዊ፤ባህላዊና ሀይማኖታዊ ገፅታ ታዋቂነትን ያተረፈ ጥንታዊ መስጂድ ነው፡፡መስጂዱ የተሰራበት 3 ሜትር መጠነ ዙሪያ ያለው ምሶሶ ከረጂም ርቀት በሰው ጉልበት ተጎትቶ መምጣቱና ከምሶሶው የሚነሱ ወጋግራዎች ውስጡን ገብቶ የሚጎበኝ ሰው ሳይደነቅባቸው ከማያልፋቸው ቅርሶች ውስጥ ተጠቃሸ ነው ፡፡መሰጀዱን ለመጎብኘት ስመጡ ከመሰጂዱ አስጎበኞች የሚነገሩ በርካታ አስገራሚ አፋታሪኮችና ገጠመኞች አሉ፡፡የስልጤ ብህረሰብ የስነ-ፁፍና ስነ-ጥብብ ሂደትን  በዉስጡ ይዞቸው በሚገኙ ባህላዊ የመፃፊያ መሳሪያዎችንና የስነ-ጥበብ ዘዬዎችን ማገንዘብ ይቻላል፡፡የአልከሶን መሰጀድና የአልከሲዬን(ሸይኩል አክበር) ታሪክ ለመመዝገብ በሄድነበት ወቅት በመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩት ሰዎች የእንግዳ አቀባበላቸው በጣም ደስ የሚል እና አስገራሚ ነበር፡፡አልከሶ መሰጀድ በወራቤ ከተማ ውስጥ ከሚገኙት የቱሪስት መስህብ ቦታዎች አንድ እና ዋነኛው ሲሆን ከማይንቀሳቀሱ ቅርሶች ውስጥ ይመደባል፡፡

የጉድሮ ደን

GEDERO DAN

የጉድሮ ተፈጥሮዊ ደን በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ በዳጤ ወዘር ቀበሌ ከከተማው ከዋናው መንገድ በሰተሰሜን አቅጣጫ 11 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ደን ስፋቱ 55.8 ሄክታር ሲሆን በተፈጥሮ ጥቅጥቅ ያለ ከጎኑ የዲጆ ወንዝ አቋርጦት የሚያልፍ እንዲሁም በውስጡ የተለያዩ አዕዋፋት፤ የዱር እንስሳት እና ዕፅዋት ይገኙበቷል፡ ፡በደኑ ውስጥ ከሚገኙት የዱር እንሰሳቶችና አዕዋፋቶች መካከል ጅብ፤ ቀበሮ፤ ሚዳቆ፤ ጥንቸል፤ አጋዘን፤ ዝንጀሮ፤ ጦጣ፤ ጃርቲ፤ ጅግራ፤ ቆቅ፤ እርግብ የመሳሰሉ እንስሳዎች እገኛሉ፡፡ በደኑ ውስጥ ከሚገኙ እፅዋቶች መካከል ፅድ፣ ሳለጊና፣ ባህር ዛፍ፣ ግራር፤ ወይራ፤ ዘንባባ፤ ዋርካ፤ ዋንዛ፤ ዚግባ… እናም የተለያዩ የሚያፈሩ ዛፎች ኢዚህ ደን ዉስጥ ይገኛሉ፡፡በደኑ ዉስጥም ሆነ በደኑም ዙሪያ ያሉ የዱር እንስሳዎችና አዕዋፋቶች የሚያፈሩት ዛፎችን በመመገብ ከጠገባቸዉ ዉኃ በመጠጣት ኑሯቸውን መሰረት አድርጎ እንቀሳቀሳሉ፡፡ ቦታውን ሲጎበኙ በአዕዋፋት ዝማሬ በነፋሻማው አየር ከፍትኛ እርካታ ያገኛሉ፡፡ ይህንን ተፈጥሯዊ ደን በመከለል፣ በማልማት፣ በመጠበቅ ለከማዉና ለሕብረተሰቡ  ትልቅ ጥቅም እንዲያገኝ ማድረግ እቻላል፡፡

የቡናር ሸለቆ

BUNAR SHELEKO

ይህ ሸለቆ በወራቤ ከተማ ከዋናው መስመር 3ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘ ሲሆን ሸለቆው በተፈጥሮው አሰራሩ በጣም የሚያሰደንቅና የሚያሰገርም ቢሆንም አካባቢውን አዕምሮዎ እሰኪላምድ ድረስ በልቦ ፍርሃት ቢጤ ይሰማዎታል፡፡ የሸለቆው አሰራር ተፈጥሯዊና አሰገራሚ ቢሆንም በሰው እጅ የተሰራ እስኪመስል ድረስ አስገራሚ አሰራር ያለው ነው፡፡ ይህን ሸለቆ ልብ ብለን ስነመለከተው የኮንሶው ኒወርክ አይነት አሰራር ያለው ነው ማለት ይቻላል፡፡በሸለቆው በር ገብቶ ወደታች ለመውርድ የቁጥቋጦዎች እገዛና ድጋፍ ከመጠየቁም በላይ በውስጡ ወይም በታችኛው ንጣፍ ለመድረስ  20 ደቂቃ ቆይታ ይጠይቃል፡፡ሸለቆውን ተፈጥሮ በራሷ ገፀ በረከቶች በማስጌጥ የተዋበ ሲሆን ከሸለቆው በታቺኛው ክፍል ሆኖ ወደ ላይ ሲታይ የመሬቱን ንጣፍ ከሰማዩ ውበት ተደምሮ ሌላ አለም ያሉ መስሎ እስኪያዩት ድረስ ውብ ነው፡፡ሸለቆው እረጂም አመታት በፊት ጠባብ፤ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ የጦር ተዋጊዎች እነደ ምሽግ ይጠቀሙበት እንደነበር የአካባቢው ማህበረሰብ በሰፋት ይናገራሉ፡፡ይህን ያህል መንገድ ከመራናችሁ ለጉብኝቱ መልካም ጉዞ እንላለን!

ያኒፋን ወንዝ

YANIFAN WENZ

ያኒ ፋን ወንዝ የሚገኘዉ በወራቤ ከተማ አስተዳደር ድሌ ዳጤ ቀበሌ ስሆን ከከተማዉ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ከድሌ ዳጤ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በስተምዕራብ 500 ሜትር ገባ ብሎ  ይገኛል፡፡ ያኒፋን ወንዝ ከስሙ ስንነሳ ትርጉሙም ያኒ ማለት በድሮ ጊዜ ባካባቢው ያኒ የሚባል አሞራ በብዛት የሚኖር ሲሆን ፋን ማለት ደግሞ ትልቅ ወንዝ ማለት ነው፡፡ይህ ወንዝ ዙሪያውን በዲንጋይ እና በእፅዋቶች የተከበበ ሲሆን ከ50 አመት በላይ እድሜ እንዳለው ይነገራል፡፡ ያኒፋን ወንዝ ጥልቀቱ ከ30-40 ሜትር ሲሆን ስፋቱ ግማሽ ሄክታር ይሆናል፡፡ በወንዙ አካባቢ ከሚገኙ የዱር እንስሳቶች መካከል አቦ ሸማኔ፣ጦጣ፣ቀበሮ፣ጢንቸል ጅብ ሲሆኑ የእፅዋቶች አይነት ደግሞ ፅድ፣ ሜሳ፣ ሽውሽዋ፣ ብሳና፣ ወይራ በተጨማሪም የተለያዩ የአዕዋፋት አይነቶች አሉ፡፡ ከነሱ መካከል አሞራ፣እርግብ፣ዋነስ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

የገንቦ(ሊፋቆ)ዋሻ

GENBO WASHA

በወራቤ ከተማ የሚገኘው የገንቦ ዋሻ በገሜ ጎጥ በዘይወት ወንዝ በሰተ ምስራቅ ከዋናው አስፓልት ከአዲስ አበባ-ወራቤ በሚወስደው መንገድ በሰተቀኝ ትንሸ ወረድ ብሎ አንድ ትልቅ መግቢያ ያለው ሲሆን ወደ ውስጥ ሲገባ በሁለት የተከፈሉ መንገዶችን አሉት፡፡በሰተምስራቅ በኩል ያለውን መንገድ ይዘን ስንጓዝ የገንቦን ዋሻ እናገኛለን፡፡ይህ ዋሻ በተወሰነ መልኩ ችግሮች አሉበተ ከችግሮቹ መካከል የመንገድ ችግር፣በአካባቢው ምግብና መጠጥ አለመኖር፣መፀዳጃ ቤት አለምኖር፣ባካባቢው ግሪን ኤርያ አለመኖር፣ የመሳስሉት ችግሮች ይታዩበታል፡፡

የጉንዳ ድልድይ

GUNDA DELDEY

የጉንዳ ተፈጥሮአዊ ድልድይ የሚገኘው በስልጤ ዞን ከወራቤ ከተማ 7 ኪ.ሜ እና ከሀዋሳ 221 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡የተፈጥሮአዊ ድልድይ ሰፋቱ ወደ 1 ሜትር ሲሆን ውሃው ከስሩ ክብ በሚመስል ቀዳዳ ሾልኮ የሚያልፍ ሲሆን የክብ ቀዳዳው ስፋት 3 ሜትር እና የድልድዩ ጥልቀት 7 ሜትር ያክል ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ የጉንዳ ድልድይ ጉንዳ የሚለውን ሰያሜ ያገኘው ድልድዩ የሚገኝበት አከባቢ (ቦታ)ስም ጉንዳ በመባል ይተወቃል፡፡ ይህ ድልድይ ከተፈጥሮ የመስህብ ቦታዎች ስመደብ ከማይንቀሳቀሱ  ቅርሶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡የጉንዳ ድልድይ ለማየት የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች አልፎ አልፎ እንደሚመጡ የአከባቢ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡የአከባቢው ሽማግሌዎች እንደሚናግሩት የደምገራን ወንዝ መፍሰስ ከቆምበት ጊዜ አንስቶ ድልድዩን የተሸከመው እንደ ምሶሶ የቆመ ድንጋይ እንዳሉ ይናግራሉ፡፡ሰው በማንኛውም ጊዜ ያለ ስጋት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንደ መሸጋገሪያነት ይጠቀሙበታል፡፡  በአከባቢው የተለያ እጽዋት እና አእዋፋት የዱር እንሰሳት ይገኛሉ፡፡ ከዱር እንስሳቶች መካከል፡-ጦጣ፣ ሚዳቆ፣ ጀብ….ከእጽዋቶች መካከል፡-ግራር ብሳና፣ ባህርዛፍ ናቸው፡፡ የተፈጥሮ ድልድይ ከሌሎች የመስህብ ቦታዎች የሚለየው ከድልድይ ስር የሚፈሰ ወንዝ እና ድልድዩ እንደመሸጋገሪያ ያገለግላል፡፡